Tuesday, January 18, 2011

ጥምቀተ እግዚእነ፤የጌታችን ጥምቀት


ጥምቀተ እግዚእነ፤የጌታችን ጥምቀት
ጌታችን እርሱ ባወቀ ለብዙ ምክንያቶች ተጠመቀ/ማቴ 3፣5-6/ዘሌ 15፣1-18/

ጥቂቶቹን እንይ

ትህትናን ሊያስተምረን- ጌታችን በደቀመዝሙሩ በፍጡሩ በዮሐንስ እጅ ባህረ ዮርዳኖስ በሰላሳ ዘመኑ ተጠምቋል፡፡ ይህን ምስጢር የፈጸመው በደቀ መዘመሩ እጅ ለመጠመቅ ወደ ነበረበት ስፍራ በመሄድ ነውና መምህረ ትህትና ያሰኘዋል፡፡

ሥርአትን ሊመሰርትልን- ሠራአ ሕግ ጌታችን ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ፤አድርጎ አድርጉ እንደሚል ደገኛ መምህር ተጠምቆ ተጠመቁ አለን፡፡

ምስጢር ሊገልጥልን- በጌታችን ጥምቀት ሰማያት ተከፍተዋል ፤የአብ ምስክርነት መንፈስቅዱስ ስምረት በርግብ አምሳል ተገልጧል፡፡ ለዚህም የሥላሴ የአካል፣ የስም የግብር ሦስትነት ተገልጧል፡፡

የእዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ- በዲያብሎስ ሥራ ተሸሽጎ የኖረውን የዕዳ ደብዳቤ እንደ ሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ ሊደመስስልን ጌታ ተጠመቀ፡፡

በአጠቃላይ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአበው ሱባኤ የተቆጠረ፣በነቢያት ትንቢት የሰፈረ መላ የሰው ልጅ ሲጠባበቀው የኖረ ልዩ ልደት ነው፡፡ የጌታችን መወለድ የሰውን ልጅ ህይወት ወደ ተፈጠረለት ዓላማ መመለስ ነው፡፡ ይህም ማለት ተወልዶ፣ተጠምቆ፣ሥጋውን ቆርሶና ደሙን አፍሶ፣ ሞትን ድል አድርጎ ዳግመኛ ህይወትን መስጠት ነው፡፡በመሆኑም በልደቱ ያገኘነውን ጸጋ በጥምቀት ልጅነት አጽንተን በመጠበቅ የመንግስቱ ወራሽ የክቡር ስሙ ቀዳሽ እንሆን ዘንድ የጌታችን ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን፡፡አሜን (ምንጭ ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ ዕትም ዘልደት ወጥምቀት 2003 ዓ.ም)

No comments:

Post a Comment