Thursday, January 27, 2011

ፅኑ ሰማአት የምነት አርበኛ


ፅኑ ሰማአት የምነት አርበኛ
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ
ቴዎድሮስ አትናትያ በስለት ያገኙሽ
ብሉይን ከሐዲስ ጠንቅቀሽ የተማርሽ
አርሴማ ልዩ ነሽ አምላክ የመረጠሽ
ፅኑ ሰማአት የምነት አርበኛ
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ
ውበትም ሐሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ
ንብረት ትዳር ሁሉ አላፊ ውአቱ
ንግስት መባልን በፍፁም ሳትሻ
አለምን በመናቅ ገባች ወደ ዋሻ
ፅኑ ሰማአት የምነት አርበኛ
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ
አረመኔው ድርታድስ ብያሰቃይሽም
ሕይወቴ ክርስቶስ ነው ብለሽ ሰበክሽ
አንገትሽን ለሰይፍ አሳልፈሽ ሰጠሽ
አርሴማ ልዩ ነሽ አምላክ የመረጠሽ
ይህን ዓለም ድል መንሳት አቅቶናልና
አርሴማ ፀልይ በምነት አንድንፀና
ስምሽን ለጠሩ ዝክርሽን ለዘከሩ
በቃልኪዳንሽ ተማምነው ኤግዚአብሔርን ለጠሩ
ሀሳባቸው ሰምሮ ይኖራሉ አንደዘመሩ
አግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ ያደረሰን
በቅዱሳኑ ፀሎት ከወደቅንበት ያነሳን
አሁንም አላለው አግዚአብሔር ይመስገን.

No comments:

Post a Comment