Monday, January 3, 2011

ገድል

መግቢያ
ገድለ ቅድስት አርሴማ
ገድል  እኔን መከተል የሜወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል  ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋት ሁሉ ያገኛታል *ማቴ ፲፮/፪፬  ባለው መሰረት ስለ ክርስቶስ ስም በእሳት ተቃጥለው በድንጋይ ተወግረው ተገርፈው በባህርና በገደል ተጥለው ለአራዊት ተሰተው በልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራ ተፈትነውና ተሰቃይተው በሰይፍ ተከልለው የሞቱትን የቅዱሳን ሰማእታትን የሂወት ታሪክ የሚነግር መንፈሳዊ መጸሃፍ ነው ገድል የወንጌል ቃል በስራ የሚገለጥበት ስለሆነ የወንጌል ፍሬ የወንጌል መታወቂያ ይባላል።
በዚህ ገድል ውስጥ ከዘመነ ሃዋርያት ጀምሮ እስከ ዘመነ ሰማእታት ድረስ ስለ ክርስቶስ ስም የቀረበላቸውን ጸዋትወ መከራ በደስታ እየተቀበሉ የሰማእትነትን ክብር የተቀዳጁ ቅዱሳን አበውና ቅዱሳት እናቶች እልፍ አእላፍ ናቸው።
የዚህ ገድል ተሳታፊ የሆኑ ቅዱሳን ሁሉ ማህበረ ነብያት ማህበረ ሃዋርያት ማህበረ ጻድቃን ማህበረ ሰማእታት ማህበረ ደናግል  ወመነኮሳት ተብለው ይጠራሉ ቅድስት ሰማእት አርሴማም በዚህ አንድነት ውስጥ ገብታ ትጠራለች።
የገድል መጸሃፍ በሰው ፍላጎትና ፈቃድ ብቻ የሚከናወን አይደለም እግዚአብሄር አምላክ በነብዩ ዳዊት አድሮ ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያነየ ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን ገባው  መዝ ፹፰/ ፫ ሲል እንደተናገረ ህጉንና ትእዛዙን ከሚተብቁ ወዳጆቹ ጋር ሊያደርገው የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ወዶ ቃል ኪዳን ገብቶአል።
ስለሆነም እግዚአብሄር አምላክ;
ሀ፣ ከቅዱሳኑ ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ለመግለጽ
ለ፣የእግዚአብሄርን ድንቅ ስራ ለመመስከር
ሐ፣የቅዱሳን ድንቅ ተጋድሎ ደግ ስራ ለማስተማሪያነት እንዲጠቅም ለማድረግ
መ፣ለሃይማኖትት ጽናት መስዋትነት ለከፈሉ ቅዱሳን አበውና ቅዱሳት እናቶች ክብር ለመስጠት
ሠ፣የሰማእትነትን የቅድስናን የተጋድሎን ቆራጥነት አርአያ ለማሳየት
ረ፣ቅዱሳን በአጸደ ስጋም ሆነ በአጸደ ነፍስ ሆነው በአለም ላሉ ወገኖቻቸው ወደ ፈታሪያቸው እያማለዱ ምህረት እንደሚያሰጡ በቅዱሳት መጻህፍት የተረጋገጠውን አጉልቶና አምልቶ ለመግለጽ
ሰ፣የእግዚአብሄር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሄር መንፈስ ያለበት መጸሃፍ ሁሉ ለትምህርትና    ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል  ፩ጢሞ ፫ ፣ ፲፮ ባለው መሰረት በመንፈስ ቅዱስ መሪነትና አጋዥነት የሚጻፍ መንፈሳዊ ታሪክ ነው።
   ይህንንም መሰረት በማድረግ ቅድስት በተክርስትያን  ቅዱሳን ሰማእታት ስለክርስቶስ የፈጸሙትን ገድል ትጽፋለች ስለ ጽድቅ የሆነውን አሟሟታቸውን በስዕል ትገልጻለች በአመት አንድ ጊዜ በአለ እረፍታቸውን ስነ ገድላቸውንና ጽቃቸውን ታስባለች መልካም ስራቸውን አርያነታቸውንና ምሳለያቸውን ለትውልድ ታስተምራለች።
ቀደምት አበው ሊቃውንት ከአምላክ በተሰታቸው ጸጋ በቅዱሳን የእረፍት ቀን ለተሰበሰቡ ምዕመናን በግዕዝ የተጻፉትን መጻህፍት እየተረጎሙና እያመሰጠሩ ሲያስተምሩና ሲመክሩ ነረዋል። ከቅዱሳን ሃዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን  ኦርቶዶክሳዊ እምነት በበጎ ምግባር ይበልጥ አጠንክረውና አክብረው ለአሁኑ ትውልድ አስተላልፈዋል።
የሰው ልጅ ሆይ አፍህ ይብላ በውስጥህም በዚህ መጸሃፍ ሆድህን ሙላ አለኝ እኔም በላሁት በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ።
ሕዝቅኤል  ፫፣፫። አንብቡት እንደ ማር ይጣፍጣል ድህነተ ነፍስም ይገኝበታል።
ከ ቅድስት አርሴማ ገድል መግቢያ የተወሰደ
አምላካችን እግዚአብሄር በቅድስት አርሴማ ቃል ኪዳን ይማረን ይቅር ይበለን መጨረሻችንን ያሳምርልን።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር
ለወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር
አሜን።

1 comment:

  1. MGM Resorts announces reopening of MGM Casino Hotel
    MGM Resorts, which 상주 출장마사지 owns and operates MGM 논산 출장마사지 Resorts International (NYSE:MGM), 대전광역 출장샵 announced on Monday it was 창원 출장마사지 reopening its MGM 통영 출장안마 Resorts casino

    ReplyDelete